am_tn/psa/072/018.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እነዚህ ጥቅሶች የዚህ መዝሙር መጨረሻ ከመሆንም በላይ ጠቀሜታ አላቸው፡፡ የመዝሙረ ዳዊት ሁለተኛ መፅሀፍ የሆነው ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 42 እስከ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 72 ድረስ ያለው መፅሀፍ የመዝጊያ ሀሳብ ነው፡፡

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ህዝብ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ይባርክ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ህዝብ የተከበረ ስሙን ለዘላለም ይባርክ” ወይም “ስም” የሚለውን ለራሱ ለእግዚአብሔር ምትክ ስም እንደሆነ በማሰብ፣ “ህዝብ እርሱ እንዴት የከበረ እንደሆነ ለዘላለም ይወቅ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የተከበረ ስሙ ይባረክ

“ክቡር የሆነው እርሱ ይባረክ”

ምድር ሁሉ በክብሩ ይሞላ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ክብሩ ምድርን ሁሉ ይሙላ” ወይም “እርሱ ምድርን ሁሉ በክብሩ ይሙላ ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አሜን፤ አሜን

አሜን የሚለው ቃል የተደጋገመው ለተነገረው ነገር ማረጋገጫመስጠቱን አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ ይህንን በመዝሙረ ዳዊት 41:13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእርግጥም እንዲህ ይሁን”

የእሴይ ልጅ የዳዊት ፀሎት እዚህ ላይ ተፈፀመ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “ዳዊት የእሴይ ልጅ ፀሎቱን ፈፀመ” ወይም “ይህ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻው ፀሎት ነው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)