1.5 KiB
1.5 KiB
ስሙ ለዘላለም ፀንቶ ይኑር
ይህ አባባል ህዝቡ ሁልጊዜ እርሱን ለማሰብ ያላቸውን ፍላጎት በመግለፅ እግዚአብሔርን ለማክበር ጥቅም ላይ ውሏል፡፡አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ሁልጊዜ ስለ እርሱ ይወቁ” ወይም “ሰዎች እርሱ ማን እንደሆነ ፈፅሞ አይርሱ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
የእርሱ ስም
እዚህ ላይ “የእርሱ ስም” የሚለው የእግዚአብሔርን መልካም ስም የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የንጉሱ ስም” ወይም “የንጉሱ መልካም ስም” ወይም “የንጉሱ ዝና” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ፀሀይ የምትኖረውን ዘመን ያህል
ግሱ ከዚህ በፊት ከነበረው ሀረግ ሊወሰድ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፀሀይ ፀንታ የምትኖረውን ያህል” ወይም “ፀሀይ እስከበራች ድረስ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)
ህዝቦች ሁሉ በእርሱ ይባረኩ
ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል። አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር እርሱ ለህዝብ መልካም ነገርን እንዲፈፅም ያድርገው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
ብሩክ ነህ ይበለው
“እግዚአብሔር እንደባረከው ይወቅ”