am_tn/psa/072/013.md

2.1 KiB

ለድኾችና ለችግረኛው ይራራል

“እርሱ ድሆችና ችግረኞች ስቃያቸውን ለማስቆም ይፈልጋል”

ድኾችና ችግረኞች

እዚህ ላይ “ድኾች” እና “`ችግረኞች” የሚሉት የስም ቅፅሎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ራሳቸውን መርዳት እንዳልቻሉ አፅንኦት የሚሰጡ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ድኾችና እነዚህ ችግረኞች የሆኑ ሰዎች” (ጥምር ቃል እና የስም ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወታቸውን ያድናል

እዚህ ላይ “ህይወት” የሚለው የሚያመለክተው የሰውን ሁለንተና ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱን አዳናቸው” ወይም “አዳናቸው” ወይም “ታደጋቸው” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

ጭቆናና ግፍ

እነዚህ ሁለት ቃላቶች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ችግረኞች ምን ያህል እንደሚሰቃዩ አፅንኦት የሚሰጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ረቂቅ ስሞች እንደ ግስ ሊብራሩ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ እነርሱን የሚጨቁኑና እነርሱን የሚጎዱ ሰዎች” (ጥምር ቃል እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ፊት ደማቸው ክቡር ነው

እዚህ ላይ “ደማቸው” የሚለው ለደህንነታቸው ምትክ ስም ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፊት ደግሞ የእርሱን ፍርድ ወይም ግምገማ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነርሱ ደህንነት ለእርሱ በጣም ዋነኛ ነገር ነው” ወይም “እነርሱ በደህንነት እንዲኖሩ ይፈልጋል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በፊቱ

ይህ ቃል በ መዝሙረ ዳዊት 19:14 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡