am_tn/psa/072/008.md

1.8 KiB

እርሱ ይግዛ

“ንጉሱ ይግዛ”

ከባህር እሰከ ባህር ድረስ፣ ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ

እነዚህ መግለጫዎች በሙሉ ወካዮቹ ሲሆኑ መላውን ምድር ያመለክታሉ፡፡ (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

ከባህር እስከ ባህር

ከሙት ባህር ጀምሮ በምስራቅ ከኪኔሬት ባህር ድረስ በምእራብ ደግሞ እስከ ሜዲቴራኒያን ባህር ድረስ፡፡

ወንዝ

“የኤፍራጥስ ወንዝ”፣ ይህ እስራኤላውያን ወደ ሰሜን አቅጣጫ በምድር የሚጓዙበት ነው፡፡

የምድር ዳርቻ

ይህ የሚያመለክተው ሰዎች ወደ ደቡብ አቅጣጫ በምድር ሊሄዱ የሚችሉበትን ርቀት በሙሉ ነው፡፡ እስራኤላውያን ምድር ዳርቻ ያላትና ዝርግ ገፅታ የያዘች እንደሆነች አድርገው ይናገራሉ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

አፈር ይልሳሉ

ይህ አባባል ተለዋጭ ዘይቤ ሲሆን ታላቅ ውርደትን የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲኖሩ ይፈቅድላቸው ዘንድ ማድረግ የሚችሉትን ማንኛውንም ነገር ያደርጋሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ታርሴስ

የቦታ ስም ነው (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ይሰጣሉ

ይከፍላሉ

ስጦታ ያቀርባሉ

“ስጦታ ይሰጣሉ”

ሳባ

ይህ የአገር ስም ነው፡፡ ይህ ከአረብ አገር ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)