am_tn/psa/072/001.md

4.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት በዕብራውያን ግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡-

የሰለሞን መዝሙር ለሚለው ርእስ አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፡- 1) ዳዊት ይህንን መዝሙር ስለ ሰለሞን ፃፈው (“የንጉሱ ወንድ ልጅ”) ወይም 2) ሰለሞን (እንደ ዳዊት ወንድ ልጅ “የንጉሱ ወንድ ልጅ” ነበር) ይህንን መዝሙር ስለ ራሱ እንደ ፀሎት ፃፈው ወይም 3) ሌላ ንጉስ በሰለሞን የአፃፃፍ ስልት ስለ ወንድ ልጁ ይህን መዝሙር ፃፈው፡፡ በእነዚህ ቀናቶች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ብዙ ጊዜ ስለ ራሳቸው ሲናገሩ ሌላ ሰው እንደሆኑ አድርገው ይናገሩ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዘማሪው ስለ ራሱ ሳይሆን ስለ ሌላ ሰው ይናገር አንደነበረ አድርጎ መተርጎም የበለጠ ተመራጭ ይሆናል፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ሆይ፣ የጽድቅ ስርአቶችህን ለንጉስ ስጥ፣ ፅድቅህን ለንጉስ ልጅ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፦ 1) “እግዚአብሔር ሆይ፣ ለእኔ ለንጉስ የፅድቅህን ስርአቶችህን ስጠኝ፣ ፅድቅህን ለልጄ” ወይም 2) “እግዚአብሔር ሆይ፣ ለእኔ ለንጉስ የፅድቅ ስርአቶችህን ስጠኝ፣ ፅድቅህን ለእኔ ለንጉስ ልጅ፡፡” በእነዚህ ቀናቶች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ብዙ ጊዜ ስለ ራሳቸው ሲናገሩ ሌላ ሰው እንደሆኑ አድርገው ይናገሩ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዘማሪው ስለራሱ ሳይሆን ስለ ሌላ ሰው ይናገር እንደነበር አድርጎ መተርጎም የበለጠ ተማራጭ ይሆናል፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

የፅድቅ ስርአቶችህን ለንጉስ ስጥ

“ንጉስ በትክክል መፍረድ እንዲችል አድርገው”

ፅድቅህን ለንጉስ ልጅ

ግሱ ከቀደመው ሀረግ ሊወሰድ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ፅድቅ የሚለው ቃል ፅድቅ ያለበት ውሳኔ ማድረግን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፅድቅህን ለንጉስ ልጅ ስጥ ወይም የንጉስ ልጅ በፅድቅ መምራት እንዲችል አድርገው” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ይፈርድ ዘንድ

ይህን የፃፈው ዳዊት ከሆነ የሚናገረው ስለ ልጁ ነው፣ “የንጉስ ልጅ” ፣ ልጁ ንጉስ የሚሆንበትን ጊዜ እየተናገረ ነው፡፡ ይህን የፃፈው ሰለሞን ከሆነ ምንም እንኳ የሚናገረው ስለ ራሱ ቢሆንም እርሱ ስለ ሌላ ሰው ይፅፍ እንደነበር አድርጎ መተርጎሙ የበለጠ ተማራጭ ነወ፡፡ በየትኛውም መንገድ ቢሆን “ንጉስ ይፈርድ ዘንድ” የሚለው የተሻለ ትርጉም ነው፡፡

ህዝብህን… ችግረኞችህን

ዘማሪው ለእግዚአብሔር እየተናገረ ነው፡፡

ችግረኞችህ

ግሱ ከበፊተኛው ሀረግ ሊወሰድ ይችላል፡፡ “ችግረኞች” የሚለው ቅፅል የሚያመለክተው ድሆችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ችግረኞች ህዝብህን ይዳኝ ዘንድ” (አስጨምሬ እና የስም ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ተራሮች የሰላምን ፍሬ ይስጡ… ኮረብቶች የፅድቅን ፍሬ ይስጡ

ዘማሪው ስለ የእስራኤል ህዝብ ሲናገር እነርሱ የሚኖሩባቸው ተራሮችና ኮረብቶች እንደሆኑ አድርጎ ገልጧቸዋል፡፡ ተራሮቹና ኮረብቶቹ የእስራኤል መላው ምድር እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፣ ይህ ምድር ደግሞ ፍሬ የሚያፈራ የአትክልት ስፍራ እንደሆነ አድርጎ በመናገር ፍሬው ደግሞ ሰላምና ፅድቅ እንደሆኑ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የምድሪቱ ህዝብ በሰላም ይኖሩ ዘንድ… ሁሉን ነገር በፅድቅ መንገድ ያደርጉ ዘንድ” (ምትክ ስም፣ ወካይ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)