am_tn/psa/071/019.md

1.3 KiB

እግዚአብሔር ሆይ ፅድቅህ ደግሞ እጅግ ታላቅ ነው

ዘማሪው እግዚአብሔር ስለሰራቸው መልካም ነገሮች ሲናገር እነዚያ ስራዎች አንድ ላይ ተሰባስበው እንደ ትልቅ ህንፃ ወይም ከፍ ያለ ተራራ እንደሆኑ ተደርጎ ተገልጧል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ አንተ ያለ ማን ነው?

ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ እንደ አረፍተ ሀሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ አንተ ያለ አንድም የለም!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ህያው አደረግኸኝ

አበረታኸኝ ወይም እንደገና እንድኖር አደረግኸኝ

ከምድር ጥልቆች

እዚህ ላይ የምድር ጥልቆች የሚለው ሰዎች ሲሞቱ ለሚሄዱበት ስፍራ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ ዘማሪው በስጋ አልሞተም ነገር ግን ይህ እርሱ የሚናገረው ግነት እንደ ሞተ አድርጎ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ሞት በምንቀርብበት ጊዜ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)