am_tn/psa/071/014.md

2.0 KiB

እጨምራለሁ

“ሁልጊዜ የበለጠ” ወይም “ሁልጊዜ ከዚህ በፊት ሳደርገው ከነበረው የበለጠ”

አፌ ፅድቅህ ይናገራ፣ ማዳንህን ደግሞ ቀኑን ሙሉ፣ ምንም እንኳ ሊገባኝ ባይችልም

“ፅድቅህን እና ማዳንህን ሙሉ በሙሉ አልተረዳሁትም፣ ነገር ግን አፌ ቀኑን ሙሉ ስለ እነርሱ ያወራል”

አፌ ይናገራል

አፍ ለሰው ሁለንተና ወካይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናገራለሁ” ወይም “በአፌ አወራለሁ እናገርማለሁ” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

ፅድቅህ

“ፅድቅ” የሚለውን ረቂቅ ስም ለማስወገድ ይህ እንደገና ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ እንዴት ፃድቅ ነህ” ወይም “የሰራሀቸው መልካም ነገሮች በሙሉ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ማዳንህ

“ማዳን” የሚለው ረቂቅ ስም አንደ ተግባር ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ እኔን እንዴት አዳንከኝ” ወይም “ሰዎችን እንዴት አዳንህ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እመጣለሁ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ሰዎች እግዚአብሔርን ወደሚያመልኩበት ስፍራ እሄዳለሁ” ወይም 2) “ወደ ጠላቶቼ እሄዳለሁ (ሂድ እና ና የሚለውን ይመልከቱ)

በጌታ በእግዚአብሔር ታላቅ ስራ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ጌታ እግዚአብሔር የሰራቸውን ታላላቅ ስራዎች ለእነርሱ እነግራቸዋለሁ” ወይም 2) ጌታ እግዚአብሔር ታላላቅ ስራዎችን ለመስራት ብርታት ስለሰጠኝ”

አስባለሁ

“ስለዚያ አወራለሁ”