am_tn/psa/071/008.md

2.2 KiB

አፌ ሁልጊዜ በምስጋናህ ይሞላል… በክብርህ

ዘማሪው በሚናገረው ቃላቶች እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማክበር ያለውን ፍላጎት ሲናገር አፉ በምግብ እንደሚሞላ እንደዚሁ በቃላቶች እንደተሞላ አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አፌ አንተን በሚያመሰግኑና በሚያከብሩ ቃላቶች ይሞላል” ወይም “እኔ ሁልጊዜ አመሰግንሀለሁ… እኔ ሁልጊዜ አከብርሀለሁ” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ምስጋና

እዚህ ላይ “ምስጋና” የሚለው እግዚአብሔርን ለማመስገን የሚጠቀምባቸውን ቃላቶች ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ምን ያህል ታላቅ እንደሆንህ ለሰዎች የሚናገሩ ቃላቶች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ክብር

እዚህ ላይ ክብር የሚለው እግዚአብሔርን ለማክበር የሚጠቀምባቸውን ቃላቶች ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች አንተን እንዲያከብሩ የሚያደርጉ ቃላቶች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ቀኑን በሙሉ

“ቀኑን ሁሉ” ወይም “ሁልጊዜ”

አትጣለኝ… አትተወኝ

እነዚህ ሁለት ቃላቶች በመሰረታዊነተ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ጥቅም ላይ የዋሉት ለአፅንኦት ነው፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

አትጣለኝ

“ከአንተ ርቄ እንድሄድ አታድርገኝ፡፡” እግዚአብሔርን እርሱን መተዉ ከእርሱ ርቆ እንዲሄድ እግዚአብሔር እንዳስገደደው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህን በ መዝሙረ ዳዊት 51:11 እንዴት እደተረጎምከው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አታስወግደኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አትተወኝ

“ሁልጊዜ አትልቀቀኝ”