am_tn/psa/071/001.md

3.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት በዕብራይስጥ ግጥም በጣም የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡-

ይህ መዝሙር ለእርዳታ የተደረገ ፀሎት ነው፡፡

እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ በአንተ እሸሸጋለሁ

ለጥበቃ ወደ እግዚአብሔር መሄድ በእርሱ እንደመሸሸግ ተደርጎ ተረግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ሆይ፣ ለጥበቃ ወደ አንተ መጣሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለዘላለም አልፈር

ይህ በገቢር ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ “ለዘላለም አልፈር” የሚለው በ መዝሙረ ዳዊት 25:2 ላይ አንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶች ፈፅሞ ለሀፍረት አይዳርጉኝ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በፅድቅህ አድነኝ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) አድነኝ ምክንያቱም አንተ ሁልጊዜ የምትሰራው ትክክለኝ የሆነውን ነገር ነው” ወይም 2) አድነኝ እኔ የምሰራው አንተ ልሰራ የምትፈልገውን ነገር ነውና (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ጆሮህን ወደ እኔ መልስ

እዚህ ላይ ጆሮህ የሚለው የሚያመለክተው ወደ እርሱ የሚፀልየውን ሰው ለመስማት የእግዚአብሔርን ፈቃደኝነት ነው፡፡ ይህን በ መዝሙረ ዳዊት 17:6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእኔ ትኩረት ስጥ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ለእኔ የመሸሸጊያ አለት ሁነኝ

ዘማሪው ጠላቶች ሊያገኙት በማይችሉበት በትልቅ አለት ገደል ውስጥ ተደብቆ ደህና ሊሆን እንደሚችል ሁሉ እንደዚሁ በደህንነት እንዲጠብቀው እግዚአብሔርን ይጠይቃል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አለት… አለት

እነዚህ አንድ ሰው እጁን በሌላው ይዞ አስገብቶ የሚይዝባቸው ኮረብቶችና ተራሮች ናቸው፣ አለቶች አይደሉም፡፡

አንተ ትእዛዝ ሰጥተሀል

“አንተ ለመላእክትህ ትእዛዝ ሰጥተሀል”

አድነኝ

“በደህንነት ጠብቀኝ”

አንተ አለቴ እና መጠጊያዬ ነህ

ዘማሪው እግዚአብሔር እንደሚጠብቀውና በትልቁ ተራራ ጫፍ ላይ እንደተደበቀና በሰው ሰራሽ መጠጊያ እንደተደበቀ ያህል እግዚአብሔር እንዲጠብቀውና ደህና እንዲያደርገው ያምናል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)