am_tn/psa/070/004.md

2.9 KiB

የሚፈልጉህ

እግዚአብሔርን መፈለግ የሚከተሉትን ሊወክል ይችላል፡- 1) እግዚአብሔርን ለእርዳታ መጠየቅ ወይም 2) ስለ እግዚአብሔር ማሰብና እርሱን መታዘዝ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን ለእርዳታ እጠይቃለሁ” ወይም “ስለ አንተ አስባለሁ እታዘዛለሁም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሀሴት ማድረግና ደስ መሰኘት

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን የደስታውን ጥልቀት አፅንኦት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በታላቅ ሁኔታ ሀሴት ማድረግ” ወይም “በጣም ደስ መሰኘት” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

መዳንህን የሚወድዱ

“መዳን” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ተግባር ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱን ስላዳንካቸው እወድሀለሁ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ሁልጊዜ ይበሉ

ይህ ግነት አፅንኦት የሚሰጠው እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ማድነቅ አስፈላጊ እንደሆነ ነው፡፡ (ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ

ይህ በገቢር መልክ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁሉም ሰው እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ችግረኛና ምስኪን

እዚህ ላይ ችግረኛ እና ምስኪን የሚሉት ቃላቶች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ራሱን መርዳት እንደማይችል አፅንኦት የሚሰጡ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም ምስኪን” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ለእኔ ፍጠን

ጸሐፊው ስለ እግዚአብሔር ሲናገር እርሱን ለመርዳት ወደ ጸሐፊው እንደሚሮጥ አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ና” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ረዳቴ ነህ፣ እኔን ታድገኸኛል

እዚህ ላይ “እኔን ታድገኸኛል” የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር እንዴት የእርሱ “ረዳት” እንደሆነ አፅንኦት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔን በመታደግ ትረዳኛለህ” (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

አትዘግይ

ይህ በገቢር ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እባክህ በፍጥነት ና” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)