am_tn/psa/066/019.md

1.7 KiB

ነገር ግን እግዚአብሔር በእውነት ሰምቶኛል፤ ትኩረት ሰጥቶኛል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በአንድ ላይ ጥቅም ላይ የዋሉት እግዚአብሔር ፀሎቱን እንዲሰማለት አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን እግዚአብሔር በእውነት ፀሎቴን ሰምቷል” (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

የፀሎቴን ድምፅ

እዚህ ላይ የጸሐፊው ፀሎት የድምፅ ግላዊ ማንነት ተሰጥቶታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፀሎቴ” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ፀሎቴን ያልከለከለኝ

እዚህ ላይ “ያልከለከለኝ” የሚለው ፀሎቱን ችላ ማለትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ”ፀሎቴን ችላ ያላለ”

ወይም የቃል ኪዳን ታማኝነቱን ከእኔ

“ከእኔ አልከለከለም” የሚለው ሀረግ ከዚህ በፊት ከነበረው ሀረግ መረዳት ይቻላል፣ እዚህ ደግሞ ሊደገም ይችላል፡፡ “የቃል ኪዳን ታማኝነት” የሚለው ሀሳብ “ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ነው” በሚለው ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የቃል ኪዳኑን ታማኝነት ከእኔ አልመለሰም” ወይም” ከእኔ ጋር ለነበረው ቃል ኪዳን ታማኝ መሆኑን አላቆመም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)