am_tn/psa/066/010.md

1.8 KiB

አንተ ወደ መረብ አመጣኸን

ጸሐፊው የእግዚአብሄር ቅጣትን እግዚአብሔር ህዝቡን በመረብ እንደያዘ አድርጎ ይናገረዋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መረብ

ለወፍ ወይም ለእንስሳ ወጥመድ

አንተ በጀርባችን ላይ ከባድ ሸክምን አስቀመጥህ

ጸሐፊው ህዝቡ የተቋቋመውን በእነርሱ ጀርባ ላይ ከባድ ጭነት መሸከም እንዳለባቸው አድርጎ ይናገረዋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲጋልቡ አደረግህ

ይህ በጦርነት ውስጥ ክፉኛ የመሸነፍ ምስል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ የእኛ ጠላቶች በጦርነት አሸንፈውን እና ከዛም በወደቀው ሰውነታችን ላይ ሰረገላቸውን እንደነዱብን እንደዛ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእሳት እና በውሀ ውስጥ ማለፍ

እግዚአብሄር እነርሱን እንደ እሳት እና ጎርፍ ባሉ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ፈተናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእሳት እና ጎርፍ እንደሚሰቃዩ ሰዎች እኛም ተሰቃየን” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰፊ ቦታ

ጸሐፊው የእስራኤል ህዝብ አሁን ስላለው በረከት ሲናገር አስተማማኝ ድነት በሚኖራቸው በሰፊና ክፍት ስፍራ እንዲመጡ እንደተደረገ አድርጎ ገልፆታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በደህንነት በምንኖርበት በክፍት ስፍራ”(ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)