am_tn/psa/066/003.md

968 B

ስራህ እንዴት አስደናቂ ነው

የእግዚአብሔር ስራዎች እኛ በአክብሮት እና በፍርሀት ውስጥ እንድንሆን ያደርጉናል ምክንያቱም እርሱ ሀይለኛ እና ቅዱስ እንደሆነ እናውቃለን፡፡

በሀይልህ ታላቅነት

“ምክንያቱም አንተ ትልቅ ሀይል አለህ”

ምድሩ ሁሉ አንተን ያመልካሉ

ይህ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ሁሉ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንተን ያመልካሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ለአንተ ስም ይዘምራሉ

እዚህ ላይ “የአንተ ስም” እግዚአብሔር ራሱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ አንተን ያመልካሉ ያከብራሉም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)