am_tn/psa/065/004.md

1.4 KiB

አንተ የመረጥከው… የአንተ ሕዝብ

አንተ እና የአንተ የሚሉት ቃላት በዚህ ጥቅስ ውስጥ እግዚአብሔርን ያመለክታሉ፡፡

በአንተ ቤተ መንግስቶች ውስጥ መኖር

ይህ ግነት ያ ሰው እግዚአብሔርን ለማምለክ በጣም አዘውትሮ ቤተ መቅደስ ውስጥ እንደሚሆን ይገልፃል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ ጊዜ በአንተ ቤተ መንግስትህ ውስጥ ማምለክ” (ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከቤትህ በረከት እንረካለን፣ ከተቀደሰው ቤተ መቅደስህም

ይህ በገቢር/አድራጊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የቤትህ በረከት፣ የተቀደሰውም ቤተ መቅደስህ እኛን ያረካናል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ እንሆናለን

እዚህ ላይ እኛ የሚለው ቃል ዳዊት እና የእስራኤል ህዝብን ያመለክታል፣ እርሱ የሚያናግረውን እግዚአብሔርን ግን አይደለም፡፡ (አግላይ እና አካታች “እኛ” የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ቤት፣ የአንተ ቅዱስ ቤተ መቅደስ

“የተቀደሰ ቤተ መቅደስህ የሆነው የአንተ ቤት”