am_tn/psa/065/001.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት በዕብራውያን ግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡-

ይህ መዝሙር የምስጋና መዝሙር ነው፡፡

ለመዘምራን አለቃ

“ይህ ለመዘምራኑ መሪ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ነው፡፡”

መዝሙር፡፡ የዳዊት መዝሙር

“ይህ ዳዊት የፃፈው መዝሙር ነው”

ለአንተ፣ በፅዮን ላለህ እግዚአብሔር፣ ምስጋናችን ይገባሀል

ይህ ምስጋና በገዛ ራሱ መተግበር የሚችል ግለሰብ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለአንተ ብቻ በፅዮን ላለህ እግዚአብሔር ምስጋናችንን እናቀርባለን” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ስዕለታችንን ለአንተ እናደርሳለን

ይህ በገቢር/አደራጊ መልኩ መገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናደርጋለን ብለን ለአንተቃል የገባነውን እናደርጋለን” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ኀጢአት በእኛ ላይ በረታብን

ዳዊች ስለ ሀጢአት ሊያሸንፍ ወይም ሊጨቁን የሚችል ግለሰብ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የገዛ ራሳችን ሀጢአት እንደሚያሸንፈን ልክ እንደዚያ ነው” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን ይቅር ትላቸዋለህ

“እነርሱ” የሚለው ቃል የእኛ “ሀጢአትን” ያመለክታል፡፡