am_tn/psa/064/001.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት በዕብራውያን ግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡-

ይህ መዝሙር ለእርዳታ ፀሎት ነው፡፡

ለመዘምራን አለቃ

“ይህ ለመዘምራኑ መሪ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ነው፡፡”

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ዳዊት መዝሙሩን ፅፎታል ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት ዘይቤ ነው

ማቆየት

ማዳን

ከክፉዎች ሚስጢራዊ ሴራ ሰውረኝ

እዚህ ላይ “መሰወር” ጥበቃን ይወክላል እናም “የክፉዎች ሚስጥራዊ ሴራ” ክፉዎች በሚስጥር ዳዊት ላይ ሊያረጉበት ያቀዱትን ጉዳት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉዎች በሚስጥር እኔ ላይ ሊያደርጉ ከአቀዱት ጉዳት ጠብቀኝ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ከአመፅ

“ሰውረኝ” የሚለው ቃል በፊተኛው ሀረግ ግልፅ ሆኗል እናም እዚህ መድገም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከአመፅ ሰውረኝ” ወይም “ከአመፅ ጠብቀኝ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

የጭካኔ አድራጊዎች አመፅ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- “አመፅ” የሚያመለክተው 1) በጩኸት የተሞላ ረብሻ አማራጭ ትርጉም፡- “ጭካኔ አድራጊዎች የሚያደርጉት በጩኸት የተሞላ ረብሻ” ወይም 2) በጩኸት የተሞላን ረብሻ የሚያደርግ ህዝብ ስብስብ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጩኸት የተሞላ የጭካኔ አድራጊዎች ህዝብ ስብስብ”