am_tn/psa/063/009.md

1.6 KiB

ወደ ምድር ጥልቅ ክፍል ውሰጥ ይወርዳሉ

ይህ ማለት ይሞቱ እና ወደ ሙታን መኖሪያ ይሄዳሉ፡፡ ይህ በትርጉም ውስጥ በግልፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሞተው ወደ ሙታን መኖሪያ ይወርዳሉ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እጃቸው ሰይፍን ለሚጠቀሙ ለእነርሱ ታልፈው ይሰጣሉ

እዚህ ላይ “ሰይፍ” በጦርነት ውስጥ ሞትን ይወክላል እና “እጃቸው ሰይፍን ለሚጠቀሙ ለእነርሱ” በጦርነት ውስጥ የሚገሏቸውን ጠላቶቻቸውን ይወክላል፡፡ ይህ በገቢር/አድራጊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር በጦርነት ውስጥ እንዲሞቱ ያደርጋል” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ለቀበሮዎች ምግብ ይሆናሉ

እዚህ ላይ “እነርሱ” በጦርነት የሞቱትን የእነርሱን ሬሳ ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቀበሮዎች ሙት ሰውነታቸውን ይበሉታል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀበሮዎቹ the

እዚህ ላይ “ቀበሮዎች” ረጅም እግር ያላቸው የዱር ውሻ አይነት ናቸው፡፡ የበሰበሰ ስጋ፣ የአደን እንስሳትን እና ፍራፍሬ ይመገባሉ፡፡