am_tn/psa/063/005.md

1.3 KiB

የመቅኒ እና ስብ ማዕድ እንደተመገብኩ እንደዚያ ይሆናል

እዚህ ላይ ጸሐፊው እግዚአብሔርን ማወቅ እና ማምለክ መልካም ማዕድን ከመብላት ይበልጥ የሚያረካ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስብ እና የተመረጠ ምግብን ከበላ ሰው ይበልጥ ደስተኛ እሆናለሁ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በደስታ በተሞሉ ከንፈሮቼ አፌ አንተን ያመሰግናል

እዚህ ላይ “በደስታ የተሞሉ ከንፈሮቼ ኣአፌ” የሚለው እግዚአብሔርን በደስታ የሚያመሰግኑትን ግለሰቦች በሙሉ ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በደስታ አመሰግንሀለሁ” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

በመኝታዬ ላይ ስለ አንደ ባሰብሁ ጊዜ….በለሊቱ ጊዜ ውስጥ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች አንደ አይነት ትርጉም አላቸው፡፡ ሀሳቦቹ ጸሐፊው ምን ያህል ስለ እግዚአብሔር እንደሚያስብ አፅንዖት ለመስጠት ነው የተደጋገሙት፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)