am_tn/psa/063/003.md

1.1 KiB

የአንተ ቃልኪዳን ታማኝነት ከህይወት የተሻለ ስለሆነ ከንፈሮቼ

“ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም በተውሳከ ግስ ሊተረጎም ይችላል እና “ህይወት” የሚለው ረቂቅ ስም በግስ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ለቃልኪዳንህ ታማኝ መሆንህን በህይወት መኖርን ከምሰጠው በላይ ከፍ ያለ ቦታ እሰጠዋለሁ ስለዚህ ከንፈሮቼ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከንፈሮቼ ያመሰግኑሀል

እዚህ ላይ “ከንፈሮቼ” ሙሉ ግለሰቡን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን አመሰግንሀለሁ” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ስም እጆቼን ወደላይ አነሳለሁ

እዚህ ላይ “በአንተ ስም” “ለአንተ” ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን አመልካለሁ ለአንተም እፀልያለሁ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)