am_tn/psa/063/001.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት/ተመሳሳይነት በዕብራውያን ግጥም የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ዳዊት መዝሙሩን ፅፎታል ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት ዘይቤ ነው

በቅንነት

በእውነተኛነት

ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ ስጋዬም አንተን ናፈቀች

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ አንድ አይነት ትርጉም አላቸው እንዴት ጸሐፊው ያለቅጥ ከእግዚአብሔር ጋር መሆን እንደሚሻ አፅንዶት ለመስጠትም ባንድነት ይጠቀማሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሙሉ ሰውነቴ ያለቅጥ ከአንተ ጋር መሆንን ይሻል” (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

በደረቅ እና አድካሚ ምድር

“ሞቃት፣ ደረቅ በረሀ”