am_tn/psa/061/006.md

1.4 KiB

ታረዝማለህ……….ብዙ ትውልዶችን

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሀሳቡ የተደጋገመው ለአፅንኦት ነው፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

የንጉሱን እድሜ ታረዝማለህ

“የንጉሱን ህይወት ትቀጥላለህ” ወይም “የንጉሱ ህይወት ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ታደርጋለህ”

የእርሱ አመታትም እንደ ብዙ ትውልዶች ይሆናሉ

እዚህ ላይ “አመታት” ምን ያህል ንጉሱ እንደሚኖር ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ለብዙ ትውልዶች ይኖራል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ለዘልአለም በእግዚአብሔር ፊት ይኖራል

እዚህ ላይ “በእግዚአብሔር ፊት መኖር” በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መሆን ወይም ከእግዚአብሔር ጋር መሆን ማለት ነው፡፡ ይህ በትርጉሙ ውስጥ በግልፅ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ለዘልአለም ከእርሱ ጋር ይሆናል” ወይም “እግዚአብሔር ለዘልአለም ከንጉሱ ጋር ይሆናል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)