am_tn/psa/061/001.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት/ተመሳሳይነት በዕብራውያን ግጥም የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡-

ይህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት ነው፡፡

ለመዘምራን አለቃ

“ይህ አምልኮ ላይ እንዲጠቀምበት ለመዘምራኑ አለቃ ነው፡፡”

ክር ባለው የሙዚቃ መሳሪያ

“ሰዎች ይህንን መዝሙር ክር ባለው የሙዚቃ መሳሪያ መጫወት አለባቸው”

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ዳዊት መዝሙሩን ፅፎታል ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) መዝሙሩ በዳዊት ዘይቤ ነው

ጩኸቴን ስማ እግዚአብሔር ሆይ፣ ፀሎቴንም አድምጥ

እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ሆይ አድምጠኝ ፀሎቴንም መልስ” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከእኔ ይልቅ ከፈ ወዳለው አለት ምራኝ

እዚህ ላይ ጸሐፊው እግዚአብሔር እርሱ ለመጠለል ወደላይ ሊወጣ የሚችልበት ከፍ ያለ አለት እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በጠላት ፊት ፅኑ ግንብ

እዚህ ላይ ጸሐፊው ስለ እግዚአብሔር እርሱ ከጠላቶቹ መከለያን የሚያቀርብ “ፅኑ ግንብ” እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከጠላቶቼ የሚከልለኝ ፅኑ ግንብ” ወይም “ከጠላቶቼ ጠብቆ እንደሚያቆየኝ ፅኑ ግንብ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)