am_tn/psa/060/010.md

1.7 KiB

እግዚአብሔር ግን፣ የጣልከን አንተ አይደለህምን?

መዝሙረኛው ይህንን ጥያቄ እግዚአብሔር የጣላቸው ስለሚመስል ስለዚያ ሀዘኑን ለመግለፅ ተጠቅሞበታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ግን እግዚአብሔር ሆይ አንተ እንደጣልከን እንደዚያ ይመስላል” ወይም “እግዚአብሔር አንተ የተውከን ይመስላል፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ከሰራዊታችን ጋር ወደ ጦርነት አትወጣህም

መዝሙረኛው እግዚአብሔር የእነርሱን ሰራዊት መርዳቱ እግዚአብሔር ሄዶ ከእነርሱ ጋር እንደሚዋጋ እንደዚያ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ጦርነት ስንሄድ ሰራዊታችንን አንተ አትረዳም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከንቱ ነው

“ዋጋቢስ ነው”

ድል ማድረግ ይሆናል

ጠላታችንን እናሸንፋለን

እርሱ ጠላቶቻችንን ይረጋግጣል

መዝሙረኛው እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን እንዲያሸንፉ የእነርሱን ሰራዊት መርዳቱ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን እንደሚረጋግጥ እንደዚያ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ጠላቶቻችንን እንድንረጋግጥ ያስችለናል” ወይም “እርሱ ጠላቶቻችንን ለማሸነፍ ብቁ ያደርገናል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)