am_tn/psa/060/004.md

2.3 KiB

አንተ ምልክትን አቆምህ

እግዚአብሔር ህዝቡን በጦርነት ውስጥ መምራቱ እግዚአብሔር ለጦር ሰራዊቱ ምልክትን ያቆመ ስጋለባሽ ንጉስ ወይም የጦር ዋና አዛዥ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ምልክትን እንዳቆመ ንጉስ እንደዚያ ነህ” ወይም “ምልክትን ወደላይ ከፍ እንደአደረገ ንጉስ እንደዚያው አንተ በጦርነት ውስጥ ትዕዛዝ ትሰጠናለህ፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምልክት

“የጦርነት ሰንደቅ አላማ፡፡” ይህ ንጉስ ወይም የጦር ዋና አዛዥ ሰራዊቱ መሰብሰብ እንዳለበት ለማሳየት በዋልታ ላይ ከፍ የሚያደርገው ሰንደቅ አላማ ነው፡፡

ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ

ይህ በገቢር/አድራጊ ሀረግ መግለፅ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ እትሞች ስለዚህ ሀረግ የተለያየ ፍቺ አላቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ “ቀስትን ከተሸከሙ ሰዎች ፊት ያመልጡ ዘንድ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀስትን ከተሸከሙ ሰዎች ፊት ያመልጡ ዘንድ

“ቀስትን የተሸከሙ ሰዎች” የሚለው ሀረግ በጦርነት ውስጥ ያሉትን የጠላት ወታደሮችን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ በጠላቶቻችሁ ላይ ወታደሮቹን ወደ ጦርነት ሲያሰማራ ያመልጡ ዘንድ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ቀኝ እጅ

የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ የእርሱን ስልጣን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በስልጣንህ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

መልስን ስጠኝ answer me

እዚህ ላይ መመለስ ለእርሱ ጥያቄ ምላሽ መስጠትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔን ጥያቄ መመለስ” ወይም “ፀሎቴን መመለስ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)