am_tn/psa/060/001.md

3.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት በዕብራውያን ግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ለመዘምራን አለቃ

“ይህ አምልኮ ላይ እንዲጠቀምበት ለመዘምራኑ አለቃ ነው፡፡”

የኪዳን ጽጌ ረዳ በምሚለው ቅኝት የሚዘመር

ይህ ምናልባትም መዝሙርን ስንዘምር ምን አይነት የዜማ ቅኝት ወይም ዘይቤ መጠቀም እንዳለብን ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህንን መዝሙር “የኪዳን ፅጌሬዳ” ቅኝትን በመጠቀም ዘምር” ወይም “ይህንን መዝሙር የኪዳን ፅጌሬዳን ዘይቤ በመጠቀም ዘምር”

የኪዳን ጽጌሬዳ

ይህ “የኪዳን ፅጌሬዳ” ማለት ነው፡፡ ተርጓሚው ትርጉሙን መፃፍ ወይም ደግሞ የዕብራይስጡን ቃል መገልበጥ ይችላል፡፡ (የማይታወቁትን ተርጉም እና ቃላትን ገልብጥ ወይም ከሌላ ውሰድ የሚለውን ይመልከቱ)

ሚክታም

ሚክታም የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ትርጉም በእርግጠኝነት አይታወቅም፡፡ በምትኩ “መዝሙር” የሚለውን ቃል መጠቀም ይቻላል፡፡ ይህ እንዲህ ተብሎ ሊፃፍ ይችላል፡- “ይህ ዳዊት የፃፈው መዝሙር ነው፡፡” ይህንን በመዝሙረ ዳዊት 16:1 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት።

አራም ናሃራይም . . . አራም ዞባህ

“በሁለቱ ወንዞች መካከል የሚገኘው አራም . . . በዞባህ የሚገኘው አራማውያን ሕዝብ።” እነዚህ ቦታዎች ናቸው።(ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)

ኢዮአብ

ይህ ኢዮአብን እና እርሱ የሚመራውን የጦር ሰራዊት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኢዮአብ እና የእርሱ የጦር ሰራዊት” (ወካይ የሚለውን ይመልከቱ)

አስራ ሁለት ሺህ ኤዶማውያን

“12,000 ኤዶማውያን” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ጣልኸን

እግዚአብሔር ሰዎችን አለመቀበሉ እነእርሱን አንደጣላቸው ተደርጎ ተረግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ አልተቀበልከንም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ምሽጋችንን ጥሰህ ገባህ

እግዚአብሔር የእስራኤል ጠላቶች ምሽጋቸውን ጥሰው እንዲገቡ መፍቀዱ እርሱ ራሱ እንደፈፀመው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ጠላቶቻችን ምሽጋችንን ጥሰው እንዲገቡ ፈቅደሀል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)