am_tn/psa/059/016.md

2.0 KiB

አንተ ለእኔ ረጅም ማማና መጠጊያ ነህና

ረጃጅም ማማዎችና መጠጊያዎች ሰዎች ከጠላቶቻቸው ለመከለል የሚሄዱባቸው ቦታዎች ናቸው። ዘማሪው ለእርሱ የሚያደርግለትን ጥበቃ እግዚአብሔር ብርቱና አስተማማኝ መጠለያ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እንደ ረጅም ማማና መጠጊያ ጠብቀኸኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በጭንቀቴ ቀን

“በችግሬ ጊዜ ሁሉ”

ጉልበቴ ሆይ፣ ለአንተ ምስጋናን እዘምርልሃለሁ

“ጉልበቴ ሆይ፣ ለአንተ” እንደ አንድ አንቀጽ ሊጣመር ይችላል። አ.ት፡ “አንተ ጉልበቴ ነህ፣ ስለዚህ ምስጋናን እዘምርልሃለሁ” (Sentence Structure የሚለውን ተመልከት)

ጉልበቴ

እግዚአብሔር የዘማሪው ጉልበት መሆኑ እግዚአብሔር እርሱን መጠበቁን ይወክላል። አ.ት፡ “ጠባቂዬ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ረጅም ማማዬ ነውና

ረጃጅም ማማዎች ሰዎች ከጠላቶቻቸው ለመከለል የሚሄዱባቸው ቦታዎች ናቸው። ዘማሪው፣ እግዚአብሔር ለእርሱ የሚያደርግለትን ጥበቃ እግዚአብሔር ብርቱና አስተማማኝ መጠለያ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እንደ ረጅም ማማ ጠብቀኸኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የቃል ኪዳን ታማኝነት አምላክ

የነገር ስም የሆነው “ታማኝነት” ከቅጽል ጋር ሊተረጎም ይችላል። ይህ ለብቻው በሚቆም ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል። አ.ት፡ “ለቃል ኪዳኑ ታማኝ የሆነው እርሱ እግዚአብሔር ነው” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)