am_tn/psa/059/008.md

1.2 KiB

ትስቅባቸዋለህ

“በንቀት ትስቅባቸዋለህ” ወይም “ትሳለቅባቸዋለህ”። የማይረቡና አቅመ ቢሶች ስለሆኑ እግዚአብሔር ይስቅባቸዋል።

ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ

“ሕዝቦችን ሁሉ ታሞኛቸዋለህ” ወይም “የየሀገሩ ሕዝብ ሞኝ እንደሆኑ ታውቃለህ”

ንቀት

ማሞኘት

ጉልበቴ

እግዚአብሔር የዘማሪው ጉልበት መሆኑ የእግዚአብሔርን ጥበቃ ይወክላል። አ.ት፡ “አንተ ጉልበቴ ነህ” ወይም “አንተ ጠባቂዬ ነህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አንተ ረጅም ማማዬ ነህ

ረጅም ማማ ሰዎች ከጠላቶቻቸው ለመከለል የሚሄዱበት ስፍራ ነው። ዘማሪው እግዚአብሔር እርሱን እንደሚጠብቀው ሲናገር እግዚአብሔር ብርቱና አስተማማኝ ከለላ እንደሆነው ይመሰክራል። አ.ት፡ “እንደ ረጅም ማማ ትከልለኛለህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)