am_tn/psa/059/006.md

2.3 KiB

በምሽት ይመለሳሉ

በውስጠ ታዋቂነት ያለው “እነርሱ” የሚለው ቃል ክፉዎች ተላላፊዎችን ያመለክታል።

እንደ ውሻ ያላዝናሉ

ዘማሪው ለማጥቃት ስለሚያስፈራሩት ጠላቶቹ ሲናገር በሰዎች ላይ እንደሚያላዝኑ ወይም እንደሚጮኹ ውሾች አድርጎ ይገልጻቸዋል። አ.ት፡ “ሰዎችን ለማጥቃት ያስፈራራሉ” (Simile የሚለውን ተመልከት)

በከተማይቱ ዙሪያ ይሄዳሉ

በከተማይቱ ዙሪያ የሚሄዱበት ምክንያት በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሚያገኙትን የትኛውንም ሰው ለማጥቃት በከተማው ዙሪያ ይሄዳሉ” (Assumed Knowledge and Implicit Information የሚለውን ተመልከት)

እነሆ

እዚህ ጋ፣ “እነሆ” የሚለው ቃል ትኩረትን ወደ አንድ ነገር ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ስማ”

በአፋቸው ያገሳሉ

መጥፎ ነገር መናገር እንደ ማግሳት ተቆጥሮ ተነግሯል። እነዚህ መጥፎ ነገሮች ስድብ ወይም ማስፈራራት ሊሆኑ ይችላሉ። አ.ት፡ “መጥፎ ነገሮችን ይናገራሉ” ወይም “መጥፎ ቃላት እየተናገሩ ይጮኻሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ማግሳት

ከፍ ባለ ድምፅ ማግሳት፤ የተቃጠለ አየር ከሆድ በአፍ በኩል ከፍ ባለና በሚረብሽ ድምፅ እንዲወጣ ማድረግ

በከንፈራቸው ውስጥ ሰይፍ አለ

ክፉ ሰዎች የሚናገሯቸው የጭከና ቃላት እንደ ሰይፍ ሆነው ተነግረዋል። አ.ት፡ “ሰይፍ ሰዎችን የሚያጠፋቸውን ያህል በሰዎች ላይ ችግር የሚፈጥሩ የጭካኔ ቃላት ይናገራሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ማን ይሰማናል?

እግዚአብሔር እንደማይሰማቸውና እንደማይቀጣቸው ማመናቸውን ለማሳየት ይህ ጥያቄ ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ማንም ሊሰማን አይችልም!” ወይም “አምላክህ አይሰማንም!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)