am_tn/psa/058/009.md

2.3 KiB

የሚነደው እሾህ ድስታችሁን ሳያሰማው … እርጥቡን እሾህና የሚነደውን እሾህ

ክፉዎች በእሾህ ቅርንጫፎች ተመስለዋል፤ በእነርሱ ላይ የእግዚአብሔር ፈጣን ቅጣትም ፈጥኖ እንደሚያነዳቸው ወይም ጠራርጎ እንደሚያስወግዳቸው ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ከማብሰያው ድስት ስር በእሳት የተለኮሰውን የእሾህ ቅርንጫፍ ጠራርጎ ሊወስድ ከሚችል ዐውሎ ነፋስ ይልቅ እግዚአብሔር ክፉ ሰዎችን በፍጥነት ያጠፋቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእናንተ

ዳዊት የሚናገረው ለእግዚአብሔር ሕዝብ ስለሆነ ይህ ብዙ ቁጥር ነው። (Forms of You የሚለውን ተመልከት)

የሚቃጠለው እሾህ ሳያሰማው … እርጥቡን እሾህና የሚነደውን እሾህ

“የሚነድደው የእሾህ ቅርንጫፍ ሙቀት … የእርጥቡ እሾህ ቅርንጫፍና የሚነደው እሾህ ቅርንጫፍ

ጻድቁ በሚያይበት ጊዜ ደስ ይለዋል

“ጻድቁ” የሚለው ቃል በጥቅሉ ጻድቅ የሆኑ ሰዎችን ያመለክታል። አ.ት፡ “ጻድቅ የሆኑ ሰዎች በሚያዩበት ጊዜ ደስ ይላቸዋል” (Generic Noun Phrases የሚለውን ተመልከት)

በክፉዎቹ ደም እግሮቹን ይታጠባል

በደም ላይ በመራመዱ የአንድ ሰው እግር መርጠቡ እግሩን በደም እንደ ታጠበ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ጻድቃን እግሮቻቸውን በክፉዎች ደም ያረጥባሉ” ወይም “ጻድቃን በክፉዎች ደም ላይ ይረማመዳሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በክፉዎች ደም እግሮቹን ይታጠባል

ይህ ግነት ብዙ ቁጥር ያላቸው ክፉ ሰዎች እንደሚሞቱ ይገልጻል። አ.ት፡ “እጅግ ብዙ ሰዎች በመሞታቸው ጻድቃን በደማቸው ላይ በሚረማመዱበት ጊዜ እግሮቻቸውን በደም ያጠቡ እስኪመስሉ ድረስ ይደርሳሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Hyperbole and Generalization የሚለውን ተመልከት)