am_tn/psa/058/006.md

2.4 KiB

ጥርሶቻቸውን ስበር … የአንበሳ ደቦሎቹን ታላላቅ ጥርስ ስበር

በእነዚህ በሁለቱም ሐረጎች ውስጥ ክፉ ሰዎች አንበሳ እንደሆኑ ተደርጎ የተነገረላቸው ሲሆን ሰዎችን እንዳይገድሉ እነርሱን አቅም ማሳጣት ደግሞ ጥርሶቻቸውን እንደ መስበር ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “የሚገድሉበትን ኃይል ውሰድባቸው። ጥርሶቻቸው ተሰብሮ እንደ ወደቀባቸው ደቦል አንበሶች አቅመ ቢስ አድርጋቸው” (Paral- lelism እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ፈጥኖ እንደሚያልፍ ወራጅ ውሃ ቀልጠው እንዲጠፉ አድርጋቸው

ክፉ ሰዎች እንደ በረዶ ወይም ውሃ ተመስለው ተነግሮላቸዋል። ዳግመኛ አለመኖር እንደ መቅለጥ ወይም ወደ መሬት ውስጥ እንደመስረግ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “እንደ ወራጅ ውሃ እንዲጠፉ አድርጋቸው” ወይም “ልክ ቀልጦ ወደ መሬት ውስጥ እንደሚሰርግ በረዶ እንዲተኑ አድርጋቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Simile የሚለውን ተመልከት)

ምንም ዒላማ እንደሌላቸው ይሁኑ

“ቀስቶቻቸው ዒላማዎቻቸውን እንደሚስቱ ይሁኑ”

ቀልጦ እንደሚጠፋ ቀንድ አውጣ ይሁኑ

ዳግመኛ አለመኖር እንደ መቅለጥ ወይም መጥፋት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ክፉዎች እንደሚቀልጥና ዳግመኛ እንደማይኖር ቀንድ አውጣ ተነው ይጥፉ” (Simile የሚለውን ተመልከት)

ቀንድ አውጣ

እስራኤላውያን እንደ እርኩስ የሚቆጥሩትና በሚያመነጨው ልጋግ መሰል ነገር ላይ ሲሄድ የሚቀልጥ የሚመስል ነፍሳት

ከሴት ተወልዶ የፀሐይን ብርሃን እንደማያይ ጭንጋፍ

አለመኖር ሞቶ የተወለደ ሕፃን መምሰል እንደሆነ ተነግሯል። አ.ት፡ “በሕይወት ለመኖርና የፀሐይን ብርሃን ለማየት እንዳይችል በጣም ቀድሞ እንደ ተወለደ ሕፃን” ወይም “ሞቶ እንደ ተወለደ ሕፃን” (Simile የሚለውን ተመልከት)