am_tn/psa/058/003.md

2.3 KiB

ክፉዎች በማህፀን እያሉ እንኳን መንገድ የሳቱ ናቸው … ከመወለዳቸው ጀምሮ መንገድ ይስታሉ

ይህ በሁለት የተለያየ መንገድ የተገለጸ ተመሳሳይ አሳብ ነው። (Parallelism የሚለውን ተመልከት)

መንገድ መሳት

የተሳሳቱ ነገሮችን ማድረግ ልክ ሰዎች በመንገድ ላይ እየሄዱ እያሉ ታጥፈው በተሳሳተ መንገድ እንደሚሄዱ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “የተሳሳተ ነገሮችን ያደርጋሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መርዛቸው ልክ እንደ እባብ መርዝ ነው

ሰዎች የሚናገሯቸው ክፉ ነገሮች መርዝ እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “የእባብ መርዝ ሰውን እንደሚጎዳ ሁሉ ክፉ ቃላቸውም ችግር ይፈጥራል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Simile የሚለውን ተመልከት)

እነርሱ ልክ ጆሮዎቹን እንደሚያቆም ደንቆሮ እባብ ናቸው

ምክርን ወይም ተግሳጽን የማይሰሙ ክፉ ሰዎች ለደጋሚው ሙዚቃ ምላሽ እንደማይሰጡ እባቦች ተደርገው ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “ጆሮዎቹን እንደሚያቆም ደንቆሮ እባብ ለመስማት አይፈልጉም” (Simile የሚለውን ተመልከት)

ጆሮዎቹን የሚያቆም ደንቆሮ እባብ

ለደጋሚው ሙዚቃ ምላሽ የማይሰጠው እባብ እንዳይሰማ ጆሮው ውስጥ የሆነ ነገር እንደ ከተተ ተደርጎ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “የማይሰማ እባብ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

እባብ

የመርዘኛ እባብ ዝርያ

ደጋሚዎች

እባቡን ለመቆጣጠር በሙዚቃ የሚጫወቱ ወይም የሚዘፍኑ ሰዎች

ምንም ያህል ብልሆች መሆናቸው ልዩነት የለውም

በእባብ ላይ ድግምት የሚያደርጉት ብልህ የሆኑት በምን እንደሆነ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እባቦቹን በመቆጣጠር ጉዳይ ደጋሚዎቹ ምንም ያህል ብልኆች ቢሆኑም እንኳን” (Assumed Knowledge and Implicit Information የሚለውን ተመልከት)