am_tn/psa/058/001.md

3.4 KiB

ለሙዚቀኞቹ አለቃ

“ይህ በዝማሬ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ለሙዚቃ መሪው የተጻፈ ነው”

ለአል ታሼዝ የተዘጋጀ

ይህ ምናልባት መዝሙሩን በሚዘምሩበት ጊዜ ምን ዓይነት የሙዚቃ ስልት ወይም ቅኝት መጠቀም እንዳለባቸው ሳይነግራቸው አይቀርም። ይህንን በመዝሙር 57፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

አል ታሼዝ

ይህ “አታጥፋ” ማለት ነው። ተርጓሚዎች ትርጉሙን መጻፍ ወይም የዕብራይስጡን ቃል መቅዳት ይኖርባቸዋል። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው እና ቃላትን ቅዳ ወይም ተዋስ የሚለውን ተመልከት)

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መዝሙሩን ዳዊት ጽፎታል ወይም 2) መዝሙሩ የሚመለከተው ዳዊትን ነው ወይም 3) መዝሙሩ የዳዊትን መዝሙሮች ዘይቤ የተከተለ ነው የሚሉት ናቸው።

ሚችታም

“ሚችታም” የሚለው ቃል ትርጉሙ በእርግጠኝነት አይታወቅም። በምትኩ “መዝሙር” የሚለውን ቃል መጠቀም ይኖርብህ ይሆናል። “ዳዊት የጻፈው መዝሙር ይህ ነው” ተብሎ ሊጻፍ ይችላል። ይህንን በመዝሙር 16፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

እናንተ ገዢዎች ጽድቅን ትናገራላችሁ?

ደራሲው በጽድቅ ስለማይናገሩ ገዢዎቹን ለመገሰጽ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “እናንተ ገዢዎች ትክክለኛውን ነገር አትናገሩም!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እናንተ … የእናንተ

“እናንተ” እና “የእናንተ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ፈራጆች የሆኑ ኃያላን ሰዎችን ነው። እዚህ ጋ የእንግሊዝኛው “ዩ” ብዙ ቁጥር ነው። (Forms of You የሚለውን ተመልከት)

እናንተ ሰዎች፣ እናንተ በጽድቅ ትፈርዳላችሁ?

ደራሲው በጽድቅ የማይፈርዱትን ፈራጆች ለመገሰጽ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “እናንተ ሰዎች፣ በሕዝቡ ላይ በጽድቅ አትፈርዱም!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

አይደለም

ደራሲው ጠይቋቸው የነበሩትን ሁለቱንም ጥያቄዎች ይመልሳል።

በልባችሁ ክፋትን ታደርጋላችሁ

ልብ የሕዝቡን አሳብ ወይም ዕቅድ ያመለክታል። አ.ት፡ “በአሳባችሁ ክፋትን ታደርጋላችሁ’ ወይም “ክፉ ነገሮችን ስለማድረግ ታስባላችሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በምድሪቱ ሁሉ ላይ በእጆቻችሁ ሁከትን ታከፋፍላላችሁ

በምድሪቱ ላይ በተለያየ ስፍራ ማወክ ልክ ሁከት ዕቃ ይመስል በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንደ ማከፋፈል ወይም እንደ ማስፋፋት ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “እናንተ ራሳችሁ በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሁከት ተግባር ትፈጽማላችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)