am_tn/psa/057/009.md

2.1 KiB

እስከ ሰማያት ድረስ፣ ምህረትህ ታላቅ ነውና … ታማኝነትህ እስከ ደመና ድረስ

የእነዚህ የሁለቱም ሐረጎች ትርጉም በጣም ተመሳሳይ ነው። የእግዚአብሔር ምህረትና ታማኝነት ታላቅነት መለካት በሚችል ርቀት ተመስሎ ተነግሯል። (Parallelism እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እስከ ሰማያት ድረስ፣ ምህረትህ ታላቅ ነውና

የእግዚአብሔር ምህረት ታላቅነት መለካት በሚችል ርቀት ተመስሎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ከመሬት እስከ ሰማያት ድረስ ያለውን ርቀት ያህል ምህረትህ ታላቅ ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ታማኝነትህ እስከ ደመና ድረስ

“ታላቅ ነው” እና “ድረስ” የሚሉትን ቃላት ቀደም ብሎ ካሉት ቁጥሮች መገንዘብ ይቻላል። አ.ት፡ “እስከ ደመናት የሚደርስ ታማኝነትህ ታላቅ ነው” ወይም “ታማኝነትህ ከመሬት እስከ ደመናት ድረስ ያለውን ርቀት ያህል ታላቅ ነው” (Ellipsis እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል

እግዚአብሔር መክበሩን እንዲያሳይ ዘማሪው እየጠየቀው ነው። ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ማለት ታላቅ መሆንን ይወክላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ማለትህን አሳይ” ወይም “እግዚአብሔር ሆይ፣ በሰማያት ላይ ታላቅ መሆንህን አሳይ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ይበል

እግዚአብሔር ክብሩን እንዲያሳይ ዘማሪው እየጠየቀው ነው። አ.ት፡ “በምድር ሁሉ ላይ ክብርህን አሳይ”