am_tn/psa/057/006.md

1.6 KiB

ለእግሮቼ መረብን ዘረጉ

ጠላቶቹ እርሱን ለመያዝ ማቀዳቸው እርሱን ለማጥመድ መሬት ላይ ወጥመድ እንደ ዘረጉ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ነገሩ ጠላቶቼ እኔን ለማጥመድ መረብ የዘረጉ ይመስላል” ወይም “ሰዎች የዱር እንስሳ ለማጥመድ መረብ እንደሚዘረጉ እኔን ለመያዝ አቅደዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በፊት ለፊቴ ጉድጓድን ቆፍረዋል

ጠላቶቹ እርሱን ለመያዝ ማቀዳቸው ይወድቅበት ዘንድ ጉድጓድ እንደ ቆፈሩለት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “እንድወድቅበት ጉድጓድ የቆፈሩልኝ ያህል ይመስላል” ወይም “ልክ ሰዎች የዱር እንስሳ ለማጥመድ ጉድጓድ እንደሚቆፍሩ እኔን ለመያዝ አቅደዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነርሱ ራሳቸው በመካከሉ ወደቁ

ጠላቶቹ እርሱን ለመያዝ በሚሞክሩበት ጊዜ በእነርሱ ላይ የደረሰባቸው ጉዳት ለእርሱ ባጠመዱት ወጥመድ ውስጥ እንደ ወደቁ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “በቆፈሩልኝ ጉድጓድ ውስጥ እነርሱ ራሳቸው ወደቁ” ወይም “ነገር ግን በእኔ ላይ ለማድረግ ባቀዱት በዚያ እነርሱ ራሳቸው ተጎዱበት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)