am_tn/psa/057/004.md

2.9 KiB

ሕይወቴ በአንበሶች መካከል ነው

ዘማሪው ስለ ጠላቶቹ ሲናገር እንደ አንበሶች ይቆጥራቸዋል። አ.ት፡ “የምኖረው በጨካኝ ጠላቶች መካከል ነው” ወይም “ጨካኝ ጠላቶች እንደ አንበሳ ከብበውኛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነዚያ ሊውጡኝ የተዘጋጁት

ማጥፋት አንድን ነገር እንደ መዋጥ ወይም ጨርሶ እንደ መብላት ሆኖ ተነግሯል። አንዳንድ ትርጉሞች የዕብራይስጡ ቃል “ጨካኝ አውሬዎች” ማለት እንደሆነ ይገነዘባሉ። ሁለቱም ሥዕሎች ጠላቶቹን እንደ ዱር አውሬ አድርገው ይገልጻሉ። አ.ት፡ “እነዚያ ሊያጠፉኝ የተዘጋጁት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጥርሶቻቸው ጦርና ቀስት የሆኑ ሕዝብ

የጠላት ቀስትና ጦር እንደ አንበሳ ጥርስ ተደርጎ ተነግሯል። ዘማሪው ጠላቶቹ እንደ አንበሳ እንደሆኑ መናገሩን ቀጥሏል። አ.ት፡ “አንበሳ በሹል ጥርሶቹ እንደሚገድል በቀስትና በጦር ሌሎችን ሰዎች የሚገድሉ ሕዝቦች” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጦርና ቀስት

የእነዚህ የሁለቱም ስያሜ የጦር መሣሪያ እስከሆነ ድረስ የአንተ ባህል አንዱን ብቻ የሚያውቅ ከሆነ እርሱን ብቻ ብትጠቀም ተቀባይነት አለው። (See: Doublet)

ምላሳቸው የተሳለ ሰይፍ ነው

ምላስ አንድ ሰው የሚናገረውን ይወክላል፣ ጭካኔን የተሞሉት የጠላቶች ቃላት እንደ ሰይፍ ተቆጥረው ተነግረዋል። አ.ት፡ “ጭካኔን የተሞሉት ቃሎቻቸው እንደ ተሳሉ ሰይፎች ናቸው” ወይም “በሚናገሩት ቃል የከፋ ችግር የሚያስከትሉብኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል

እግዚአብሔር መክበሩን እንዲያሳይ ዘማሪው እየጠየቀው ነው። ከሰማያት በላይ ከፍ ማለት ታላቅ መሆንን ይወክላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ማለትህን አሳይ” ወይም “እግዚአብሔር ሆይ፣ በሰማያት ላይ ታላቅ መሆንህን አሳይ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን

እግዚአብሔር ክብሩን እንዲያሳይ ዘማሪው እየጠየቀው ነው። አ.ት፡ “በምድር ሁሉ ላይ ክብርህን አሳይ”