am_tn/psa/057/001.md

3.1 KiB

ለሙዚቀኞቹ አለቃ

“ይህ በዝማሬ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ለሙዚቃ መሪው የተጻፈ ነው”

ለአል ታሼዝ የተዘጋጀ

ይህ ምናልባት መዝሙሩን በሚዘምሩበት ጊዜ ምን ዓይነት የሙዚቃ ስልት ወይም ቅኝት መጠቀም እንዳለባቸው ሳይነግራቸው አይቀርም። አ.ት፡ “’የአል ታሼዝን ቅኝት በመጠቀም ይህንን መዝሙር ዘምሩ” ወይም “የአል ታሼዝን ስልት በመጠቀም ይህንን ዘምሩ”

አል ታሼዝ

ይህ “አታጥፋ” ማለት ነው። ተርጓሚዎች ትርጉሙን መጻፍ ወይም የዕብራይስጡን ቃል መቅዳት ይኖርባቸዋል። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው እና ቃላትን ቅዳ ወይም ተዋስ የሚለውን ተመልከት)

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መዝሙሩን ዳዊት ጽፎታል ወይም 2) መዝሙሩ የሚመለከተው ዳዊትን ነው ወይም 3) መዝሙሩ የዳዊትን መዝሙሮች ዘይቤ የተከተለ ነው የሚሉት ናቸው።

ሚችታም

“ሚችታም” የሚለው ቃል ትርጉሙ በእርግጠኝነት አይታወቅም። በምትኩ “መዝሙር” የሚለውን ቃል መጠቀም ይኖርብህ ይሆናል። “ዳዊት የጻፈው መዝሙር ይህ ነው” ተብሎ ሊጻፍ ይችላል። ይህንን በመዝሙር 16፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ከሳዖል ሸሽቶ በዋሻ ውስጥ በነበረ ጊዜ

የዚህ ሐረግ ዓላማ ሁኔታውን በዝርዝር ከሚያስረዱ አንዳንድ መሠረታዊ ነገሮች ጋር በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ይህ ዳዊት ዋሻ ውስጥ ከሳዖል ስለተደበቀበት ጊዜ ነው” ወይም “ይህ ንጉሥ ሳዖል ዳዊትን ባሳደደው ጊዜ ዳዊት ዋሻ ውስጥ ስለተደበቀበት ወቅት ነው” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

አንተን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ

ጥበቃ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር መሄድ በእርሱ መጠጊያ ማግኘት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ጥበቃ ለማግኘት ወደ አንተ እመጣለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከለላ ለማግኘት በክንፎችህ ስር እቆያለሁ

ዘማሪው ስለ እግዚአብሔር ሲናገር ጫጩቶቿን በክንፎቿ ስር ከምትሰበስባቸው ወፍ ጋር ያነጻጽረዋል። አ.ት፡ “እንደምትጠብቀኝ እታመንሃለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይህ ጥፋት እስኪያልፍ ድረስ

የነገር ስም የሆነው “ጥፋት” እንደ “አጥፊ” ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ይህ አጥፊ ማዕበል እስኪያልፍ ድረስ” (የነገር ስም እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)