am_tn/psa/056/007.md

2.3 KiB

ኃጢአትን ሠርተው እንዲያመልጡ አትተዋቸው

ካመለጡ በግልጽ ይከሰሳሉ። አ.ት፡ “ስለ ኃጢአታቸው በአንተ ከመቀጣት እንዲያመልጡ አትተዋቸው” ወይም “ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር አንተ በምትቀጣቸው ጊዜ እንዲያመልጡ አትተዋቸው” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

ሕዝቡን ጣላቸው

ጠላቶችን ማሸነፍ እነርሱን እንደ መጣል ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሕዝቡን ድል አድርጋቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መንከራተቴን ትመዘግባለህ

እግዚአብሔር ስለ ዘማሪው ግድ መሰኘቱ፣ ዘማሪው ለመጽናናት የሚሄድበት ስፍራ ሳይኖረው በስጋት የተመላለሰበትን እያንዳንዱን ጊዜ እግዚአብሔር እንደቆጠረለት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ብቻዬን ስለ ተንከራተትኩባቸው ጊዜያት ሁሉ አንተ ይገድሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዕንባዬን በጠርሙስህ አስቀምጠው

እግዚአብሔር ለዘማሪው ግድ መሰኘቱ፣ እግዚአብሔር የዘማሪውን ዕንባ በጠርሙስ ውስጥ እንዳስቀመጠ ተደርጎ ተነግሯል። ዕንባ ለቅሶን ይወክላል። አ.ት፡ “ምን ያህል እንዳለቀስኩ ታውቃለህ፣ ስለ እኔም ይገድሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመጽሐፍህ ውስጥ ያሉ አይደሉም?

እግዚአብሔር ለዘማሪው ግድ መሰኘቱ፣ እግዚአብሔር የዘማሪውን የዕንባ ቁጥር በመጽሐፉ ውስጥ እንደጻፈ ተደርጎ ተነግሯል። እግዚአብሔር ለዘማሪው እጅግ እንደሚጠነቀቅለት ለማሳሰብ ጥያቄው ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ስለ እነርሱ በመጽሐፍህ ውስጥ ጽፈሃል!” ወይም “ለቅሶዬን ታስታውሳለህ!” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)