am_tn/psa/056/005.md

1.5 KiB

ቀኑን ሁሉ

“ሁልጊዜ”

ቃሌን ያጣምማሉ

አንድ ሰው የሚናገረውን ደግሞ መናገር፣ ነገር ግን ትንሽ ለውጥ በማድረግ ሌላ ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ ቃላቸውን እንደማጣመም ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ያልተናገርኩትን እንደተናገርኩ አድርገው ይናገራሉ” ወይም “ነገሮቹን እኔ እንደ ተናገርኩ ይናገራሉ፣ ነገር ግን ይዋሻሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእኔ ላይ የሚያስቡት ሁሉ ለክፋት ነው

“በእኔ ላይ ሁልጊዜ ክፉ አሳብ አላቸው” ወይም “ክፉ ነገር ሊያደርጉብኝ ሁልጊዜ ያስባሉ”

እርምጃዬን ይከታተላሉ

ልክ አንድን ሰው ለመያዝ የሚፈልግ፣ ያ ሰው ወዴት እንደሚሄድ እንደሚመለካከት ሁሉ፣ አንድን ሰው ችግር ላይ ለመጣል እርሱ የሚያደርገውን መመልከት ርምጃውን እንደመመልከት ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “የማደርገውን ሁሉ ይመለከታሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ልክ ሕይወቴን እንደሚጠባበቋት

አንድን ሰው ለመግደል መጠባበቅ ሕይወቱን እንደ መጠባበቅ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “እኔን ለመግደል ሲጠብቁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)