am_tn/psa/056/001.md

2.2 KiB

ለሙዚቀኞቹ አለቃ

“ይህ በዝማሬ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ለሙዚቃ መሪው የተጻፈ ነው”

ለዮናስ ኤሌም ሬሆኪም የተዘጋጀ

ይህ ምናልባት መዝሙሩን በሚዘምሩበት ጊዜ ምን ዓይነት የሙዚቃ ስልት ወይም ቅኝት መጠቀም እንዳለባቸው ሳይነግራቸው አይቀርም። አ.ት፡ “’የዮናስ ኤሌም ሬሆኪም’ን ቅኝት በመጠቀም ይህንን መዝሙር ዘምሩ” ወይም “የዮናስ ኤሌም ሬሆኪምን ስልት በመጠቀም ይህንን ዘምሩ”

ዮናስ ኤሌም ሬሆኪም

ይህ ምናልባት “በሩቅ የወርካ ዛፎች ላይ ያለች እርግብ” ማለት ሊሆን ይችላል። ተርጓሚዎች ትርጉሙን መጻፍ ወይም የዕብራይስጡን ቃላት መቅዳት ይኖርባቸው ይሆናል። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው እና ቃላትን ቅዳ ወይም ተዋስ የሚለውን ተመልከት)

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መዝሙሩን ዳዊት ጽፎታል ወይም 2) መዝሙሩ የሚመለከተው ዳዊትን ነው ወይም 3) መዝሙሩ የዳዊትን መዝሙሮች ዘይቤ የተከተለ ነው የሚሉት ናቸው።

ሚችታም

“ሚችታም” የሚለው ቃል ትርጉሙ በእርግጠኝነት አይታወቅም። በምትኩ “መዝሙር” የሚለውን ቃል መጠቀም ይኖርብህ ይሆናል። “ዳዊት የጻፈው መዝሙር ይህ ነው” ተብሎ ሊጻፍ ይችላል። ይህንን በመዝሙር 16፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ፍልስጤማውያን በጌት በያዙት ጊዜ

“ፍልስጤማውያን በጌት በማረኩት ጊዜ”

ከበባቸውን አጠናክረዋል

“ሊወጉኝ በጣም ተጠግተዋል”

ጠላቶቼ ረጋግጠውኛል

የጠላት ብርቱ ጥቃት በእርሱ ላይ በመሄድ ሰውነቱን የሰባበሩት በሚመስል መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “ጠላቶቼ ክፉኛ እያጠቁኝ ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)