am_tn/psa/055/022.md

2.6 KiB

ሸክምህን አስቀምጥ

እዚህ ጋ ዘማሪው የሚናገረው ለሌሎች እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ሰዎች ነው።

ሸክማችሁን በእግዚአብሔር ላይ አስቀምጡት

እዚህ ጋ፣ ችግሮች ሰዎች እንደሚሸከሟቸው ሸክሞች ተደርገው ተነግረዋል። በችግራችን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲረዳን በእርሱ መታመናችን እርሱ ስለ እኛ እንዲሸከማቸው ሸክሞቻችንን በእርሱ ላይ እንደ መጣል ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ችግሮችህን ለእግዚአብሕር ስጠው” ወይም “አንዱ፣ ብርቱ የሆነውን ሰው ‘ሸክሜን ሊሸከምልኝ ይችላል’ ብሎ እንደሚታመነው፣ አንተም በችግሮችህ ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚረዳህ ታመነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እርሱ ይደግፍሃል

አንድ ሰው ችግር በሚገጥመው ጊዜ እርሱን መንከባከብ ወይም መርዳት እርሱን እንደ መርዳት ተቆጥሮ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “እርሱ ይጠነቀቅልሃል” ወይም “እርሱ ይረዳሃል”

ጻድቁ እንዲንገዳገድ እርሱ በፍጹም አይፈቅድም

አንድ በሆነ ዓይነት አደጋ ክፉኛ የተጎዳ ሰው ለመውደቅ እንደሚንገዳገድ ወይም እንደሚወዛወዝ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ጻድቁን ሰው ተንገዳግዶ እንዲወድቅ አይተወውም” ወይም “ጻድቁ ሰው እንዲጠፋ አይተወውም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ግን

አሁን ደራሲው የሚናገረው ለእግዚአብሔር ነው።

የጥፋት ጉድጓድ

ይህ ምናልባት መቃብርን ወይም ሲዖልን ያመለክታል።

ክፉዉን ወደ ጥፋት ጉድጓድ ውስጥ ያወርደዋል

ይህ ሰዎች እንዲሞቱ ማድረግን ይወክላል። አ.ት፡ “ክፉው እንዲሞት ያደርጋል” ወይም “ክፉ ሰዎች እንዲሞቱና ሙታን ወዳሉበት ስፍራ እንዲሄዱ ያደርጋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ደም የተጠሙና የሚያታልሉ ሰዎች

“የሚዋሹና ሌሎችን ለመግደል የሚፈልጉ ሰዎች” ወይም “አታላይ ነፍሰ ገዳዮች”

የሌሎቹን ግማሽ እንኳን

“ሌሎች ሰዎች ከሚኖሩት ግማሹን እንኳን”