am_tn/psa/055/015.md

1.5 KiB

ሞት በድንገት ይምጣባቸው

ሞት ሰዎችን ሊያጠቃ እንደሚችል ሰው ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ጠላቶቼ በድንገት ይሙቱ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ሕያዋን ሳሉ ወደ ሲዖል ይውረዱ

በድንገት መሞት ሰዎች መሞታቸው እንኳን በአግባቡ ሳይረጋገጥ በፍጥነት ወደ ሲዖል እንደሚሄዱ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “በድንገት ወደ ሲዖል ይሂዱ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ክፋት መኖሪያቸው ነው

ክፋት በሆነ ቦታ ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ነገር ተደርጎ ተነግሯል። የጠላቶቹ የተለመደው ክፋት ከእነርሱ ጋር ወይም አጠገባቸው እንደሚኖር ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “በሚኖሩበት ስፍራ ሁልጊዜ ክፉ ነገሮችን ያደርጋሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እዚያው በመካከላቸው

ይህ ሐረግ፣ ክፋት በጣም በቅርባቸው አለ የሚለውን አሳብ ያጠናክራኣል። እዚህ ጋ፣ ክፋት በቤቶቻቸው ብቻ ሳይሆን ባሉበት ቦታ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ባሉበት ቦታ ሁሉ ክፉ ነገሮችን ሁልጊዜ ያደርጋሉ” ወይም “ባሉበት ቦታ ሁሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)