am_tn/psa/055/012.md

1.4 KiB

ልሸከመው እችል ነበር

ተግሳጽን መታገስና መጽናት እርሱን ይዞ እንደመቆየትና እንደ መሸከም ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ተግሳጹን መታገስ በቻልኩ ነበር” ወይም “ስለ ተግሳጹ እምብዛም አላዝንም ነበር” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ራሱን በእኔ ላይ ቀና አደረገ

ኩሩ መሆንና ሌላውን መሳደብ ራስን በሌላው ላይ ቀና አንደማድረግ ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሰደበኝ” ወይም “ናቀኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ነገር ግን አድራጊው አንተ ነህ

እርሱን የሚገስጸውና የሚያንጓጥጠው ሰውዬ በዚያ ሆኖ ይሰማው ይመስል ዘማሪው ይናገረዋል። (See: Apostrophe)

እኔ ራሴ፣ ባልንጀራዬና የቅርብ ጓደኛዬ

ይህ ተከፋፍሎ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊጀመር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ ራሴ። አንተ ባልንጀራዬና የቅርብ ጓደኛዬ ነበርክ”

እኛ

“እኛ” የሚለው ቃል ዘማሪውንና ጓደኛውን ያመለክታል።

ከተሰበሰበው ጋር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “በአንድነት” ወይም 2) “ከሕዝቡ ጋር” የሚሉት ናቸው።