am_tn/psa/055/010.md

2.6 KiB

በግምቦቹ ላይ ይወጣሉ

“ግፍና ሁከት በግምቦቿ ላይ ይወጣሉ”። (መዝሙር 55፡9ን ተመልከት) ግፍና ሁከት እንደ ሰዎች ተቆጥረው ተነግሮላቸዋል። ግፍና ሁከትን ስለሚፈጥሩ ሰዎች ይህንን በመናገር መግለጽ ይቻላል። አ.ት፡ “በከተማይቱ ግምቦች ላይ ሰዎች እየተዋጉና እያወኩ ይመላለሳሉ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

በግምቦቿ ላይ

“በከተማይቱ ግምቦች አናት ላይ”። ከተሞች ከጠላቶቻቸው የሚጠበቁባቸው ጠንካራ ግምቦች በዙሪያቸው ይኖራቸው ነበር። የትኛውም ጠላት ወደ ከተማይቱ በመምጣት ላይ መሆኑን ለማየት ሰዎች በግምቦቹ አናት ላይ መመላለስ ይችሉ ነበር።

ኃጢአትና ተንኮል በመካከሏ ነው

ኃጢአትና ተንኮል እንደ ሰዎች ተቆጥረው ተነግሮላቸዋል። ይህንን፣ ኃጢአትንና ተንኮልን ስለሚያደርጉ ሰዎች በመናገር መግለጽ ይቻላል። አ.ት፡ “በከተማይቱ መካከል ሰዎች ኃጢአትን ይሠራሉ፣ ተንኮልንም ያደርጋሉ” ወይም “በውስጧ ሰዎች በኃጢአት የተሞሉ ነገሮችን ይሠራሉ፣ ችግርም ይፈጥራሉ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ተንኮል

ችግር

ክፋት በመካከሏ ነው

ክፋት እንደ ሰው ተቆጥሮ ተነግሮለታል። ይህንን፣ ክፉ ነገሮችን ስላደረጉ ሰዎች በመናገር መግለጽ ይቻላል። አ.ት፡ “በከተማይቱ መካከል ሰዎች ክፉ ነገሮችን ያደርጋሉ” ወይም “ሰዎች በከተማይቱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ያጠፋሉ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ግፍና ማታለል ከጎዳናዎቿ አይርቁም

ግፍና ማታለል እንደ ሰዎች ተቆጥረዋል። ይህንን በሌሎች ላይ ግፍ ስለሚያደርጉና ስለሚያታልሉ ሰዎች በመናገር መግለጽ ይቻላል። አ.ት፡ “በከተማይቱ ጎዳናዎች ሰዎች በሌሎች ላይ ግፍና ማታለልን ይፈጽማሉ፣ ከዚያም አይርቁም” ወይም “በከተማይቱ ጎዳናዎች ላይ ሰዎች ሁልጊዜ በሌሎች ላይ ግፍ ይፈጽማሉ፣ ያታልላሉ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

በጎዳናዎቿ ላይ

ይህ ምናልባት በከተማይቱ ውስጥ ያለውን የገበያ ስፍራ ያመለክት ይሆናል።