am_tn/psa/053/006.md

1.4 KiB

ምነው የእስራኤል ድነት በመጣ!

እዚህ ጋ “ምነው” የሚለው ቃል ተስፋን ወይም ጸሎትን የሚገልጽ ቃለ አጋኖን ያስተዋውቃል። አ.ት፡ “የእስራኤል ድነት እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ” ወይም “ድነት እንዲመጣ እጸልያለሁ” (ቃለ አጋኖ የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ድነት ከጽዮን ይመጣል

ድነት መቅደሱ በጽዮን የሆነውን፣ አዳኙን እግዚአብሔርን ይወክላል። አ.ት፡ “የእስራኤል አዳኝ ከጽዮን ይመጣል” ወይም “እግዚአብሔር ከጽዮን ይመጣና እስራኤልን ያድናል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ሕዝቡን ከምርኮ በሚመልስበት ጊዜ

“እግዚአብሔር የተማረከ ሕዝቡን በሚያድንበት ጊዜ”

ያዕቆብ ደስ ይለዋል፣ እስራኤልም ሐሴትን ያደርጋል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው። (See: Parallelism)

ያዕቆብ

እዚህ ጋ “ያዕቆብ” የሚያመለክተው የያዕቆብ ዘር የሆኑትን እስራኤላውያንን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)