am_tn/psa/052/004.md

1.8 KiB

ሌሎችን የሚበሉ ቃላቶችን

እዚህ ጋ ሌሎችን የሚጎዱ ቃላት ሰዎችን እንደሚበሉ የዱር እንስሶች ተደርገው ተነግረዋል። አ.ት፡ “ሌሎችን የሚጎዱ ቃላት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አንተ አታላይ ምላስ ሆይ

ይህ ደራሲው የሚናገረውን ሰውዬ ያመለክታል። አ.ት፡ “የማታለልን ቃል የምትናገር አንተ” ወይም “አንተ ውሸታም” (See: Synecdoche)

መንጥቆ ያወጣሃል … ይጎትትሃል … ይነቅልሃል

እነዚህ ሦስቱም ሐረጎች በተለያየ መንገድ “ያስወግድሃል” የሚል ትርጉም አላቸው። (See: Parallelism)

ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል

በምድር ላይ ሕያው ሆኖ መኖር፣ ሥራቸውን በመሬት ውስጥ በሚያደርጉ ተክሎች ተመስለው ስለ ሰዎች ተነግሯል። እግዚአብሔር አንድን ሰው መግደሉ ልክ የተክልን ሥር ከመሬት ውስጥ እንደ መንቀል ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ከሕያዋን ምድር ይወስድሃል” ወይም “ከሕያዋን ሰዎች ጋር በምድር ላይ እንዳትኖር ይገድልሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሴላ

ይህ ሰዎች እንዴት መዘመር ወይም የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት እንዳለባቸው የተነገራቸው ሙዚቃዊ ቃል ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ትርጉሞች የዕብራይስጡን ቃል ሲጽፉ አንዳንድ ትርጉሞች ደግሞ ይህንን አያካትቱም። (ቃላትን ቅዳ ወይም ተዋስ የሚለውን ተመልከት)