am_tn/psa/051/007.md

3.2 KiB

አንጻኝ … እነጻለሁ … እጠበኝ … ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ

በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት ንጹሕ ወይም ነጭ እንደመሆን ተቆጥሮ ተነግሯል። እግዚአብሔር የሰዎችን ኃጢአት ይቅር በማለት ተቀባይነት እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በሂሶጵ አንጻኝ

ጸሐፊው ስለ እግዚአብሔር ሲናገር፣ እርሱን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ውሃ እንደሚረጭበት ካህን አድርጎ ይገልጸዋል። አ.ት፡ “ውሃውን በሂሶጵ ነክረህ በእኔ ላይ በመርጨት ተቀባይነት እንዲኖረኝ አድርገኝ” ወይም “በአንተ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረኝ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሂሶጵ

ይህ ካህናት ለማንጻት ሥርዓት፣ ይኸውም ለእግዚአብሔር ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ፣ በሰዎች ወይም በሌሎች ነገሮች ላይ ውሃ ወይም ደም ለመርጨት የሚጠቀሙበት ተክል ነው። (See: የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)

ከበረዶ ይልቅ ነጭ

ኃጢአት የሌለበት መሆን ነጭ እንደ መሆን ተቆጥሯል። አ.ት፡ “እጅግ፣ በጣም ነጭ” (See: Simile)

ደስታና ሐሴት

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ቃላት የሚሉት አንድ ነገር ሆኖ አስደሳች ነገሮችን ለመስማት ባለው ምኞት ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet)

የሰበርካቸው አጥንቶቼ ደስ ይሰኙ ዘንድ

ስለ ተሰማው አስከፊ ሐዘን ሲገልጽ አጥንቶቹ እንደተሰበሩ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “በውሳጣዊው ማንነቴ ላይ የከፋ ሐዘን እንዲደርስብኝ አድርገሃልና። እንደገና ደስ ይበለኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ

ስለ አንድ ሰው ኃጢአት ማሰብ ኃጢአቱን እንደ ማየት ሆኖ ተነግሯል። ይቅር ማለት ወይም ኃጢአቱን ለማሰብ አለመፍቀድ ለማየትም እንዳለመፍቀድ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ኃጢአቴን አትመለከት” ወይም “ኃጢአቴን አታስታውሰው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኃጢአቴን ሁሉ ደምስስልኝ

የአንድን ሰው ኃጢአት ይቅር ማለት ወይም ለማሰብ አለመፍቀድ 1) እንደ መደምሰስ ወይም 2) በጽሑፍ የተመዘገበውን ኃጢአት እንደ መሰረዝ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ 1) “አንድ ሰው አንድን ነገር ጠርጎ እንደሚያስወግደው ኃጢአቴን ይቅር በለኝ” ወይም “አንድ ሰው የተመዘገበውን ኃጢአት እንደሚሰርዝ ኃጢአቴን እርሳው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)