am_tn/psa/051/005.md

1.8 KiB

እይ፣ የተወለድኩት በአመፅ ነው … እይ፣ አንተ ታማኝነትን ትፈልጋለህ

እዚህ ጋ፣ ሁለቱ የ “እይ” አጠቃቀሞች ትኩረታችንን በሁለቱ ሁኔታዎች መካከል ወዳለው ንጽጽር ይስቡታል። አ.ት፡ “በእውነት እኔ የተወለደኩት በአመፅ ነው … አንተ ግን ታማኝነትን ትፈልጋለህ”

እይ፣ የተወለድኩት በአመፅ ነው … እናቴ እንደ ፀነሰችኝ በኃጢአት ውስጥ ነበርኩኝ

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት አንድ ነገር ሲሆን በአንድ ላይ ጥቅም ላይ የዋሉት አጽንዖት ለመስጠት ነው። (See: Paral- lelism)

የተወለድኩት በአመፅ ነው

ኃጢአተኛ መሆን በደለኛ እንደመሆን ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “በተወለድኩ ጊዜ ወዲያው ኃጢአተኛ ሆንኩኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እናቴ እንደ ፀነሰችኝ በኃጢአት ውስጥ ነበርኩኝ

ኃጢአተኛ መሆን በኃጢአት ውስጥ እንደመሆን ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “እናቴ በፀነሰችኝ ጊዜ እንኳን እኔ ኃጢአተኛ ነበርኩ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በውስጡ ማንነቴ ታማኝ እንድሆን ትፈልጋለህ

“ውስጣዊ ማንነት” የሚወክለው 1) የሰውየውን ፍላጎት ወይም 2) ሙሉዉን ሰው ነው። አ.ት፡ “ታማኝነትን እንድመኝ ትፈልጋለህ” ወይም “ታማኝ እንድሆን ትፈልጋለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Synecdoche የሚለውን ተመልከት)