am_tn/psa/051/001.md

3.1 KiB

ለሙዚቀኞቹ አለቃ

“ይህ በዝማሬ አምልኮ ውስጥ ለመጠቀም ለሙዚቃ መሪው የተጻፈ ነው”

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) መዝሙሩን ዳዊት ጽፎታል ወይም 2) መዝሙሩ የሚመለከተው ዳዊትን ነው ወይም 3) መዝሙሩ የዳዊትን መዝሙሮች ዘይቤ የተከተለ ነው የሚሉት ናቸው።

ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ

ናታን ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ ያደረገው ነገር በግልጽ ሊነገር ይችላል፣ ምክንያቱም ይህ መዝሙር ለዚያ ምላሽ ነውና። አ.ት፡ “ነቢዩ ናታን ወደ ዳዊት መጥቶ በገሰጸው ጊዜ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

ከቤርሳቤህ ጋር ከተኛ በኋላ

“ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ከተኛ በኋላ”

ስለ ቃል ኪዳን ታማኝነትህ

የነገር ስም የሆነው “ታማኝነት” እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አንተ ለኪዳንህ ታማኝ ስለሆንክ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

እጅግ ብዙ ስለሆኑት ምሕረትን የተሞሉ ሥራዎች

“እጅግ ብዙ የምሕረት ሥራዎችን ታደርጋለህና”

መተላለፌን ደምስሰው

ኃጢአትን ይቅር ማለት 1) እንደ መደምሰስ ወይም 2) በጽሑፍ የተመዘገበውን ኃጢአት እንደ መሰረዝ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “አንድ ሰው አንድን ነገር ጠርጎ እንደሚያስወግደው ኃጢአቴን ይቅር በለኝ” ወይም “አንድ ሰው የተመዘገበውን ኃጢአት እንደሚሰርዝ ኃጢአቴን እርሳው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከበደሌ ፈጽመህ እጠበኝ … ከኃጢአቴ አንጻኝ

እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች የሚሉት አንድ ነገር ነው። (See: Parallelism)

ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ

በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት ንጹሕ እንደ መሆን ተደርጎ ተነግሯል። እግዚአብሔር የሰዎችን ኃጢአት ይቅር በማለት ተቀባይነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። አ.ት፡ “ኃጢአቴን ሁሉ እጠብልኝ” ወይም “በአንተ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረኝ ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ፈጽሞ

ሙሉ በሙሉ፣ ጨርሶ

ከኃጢአቴ አንጻኝ

በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት ንጹሕ እንደ መሆን ተደርጎ ተነግሯል። እግዚአብሔር የሰዎችን ኃጢአት ይቅር በማለት ተቀባይነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። አ.ት፡ “ከኃጢአቴ አንጻኝ” ወይም “ንጹሕ እንድሆን ኃጢአቴን ይቅር በለኝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)