am_tn/psa/050/021.md

2.0 KiB

እኔም ልክ እንዳንተው እንደሆንኩ አሰብክ

እግዚአብሔር ክፉ ሰዎችን ሳይገስጻቸው ዝም በማለቱ ምክንያት እያደረጉት ያሉትን እግዚአብሔር እንዳጸደቀላቸው አሰቡ። አ.ት፡ “ልክ አንተ እንደምታደርገው እኔም እንደማደርግ አሰብክ” (See: Assumed Knowledge እና Implicit Information የሚለውን ተመልከት)

መውቀስ

ለአንድ ሰው የማይገባውን በማድረጉ በደለኛ ስለ መሆኑ መንገር

ያደረግከውን ነገር ሁሉ … አምጣ

ያደረጉትን ክፉ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚዘረዝራቸው ይናገራል። አ.ት፡ “ያደረግከውን ነገር ሁሉ … ዘርዝር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በዐይኖችህ ፊት መልካም

እዚህ ጋ “በዐይኖችህ ፊት” መሆን ማለት ሊያዩት በሚችሉበት ቦታ ማለት ነው። ይህ ማለት እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የሚያቀርበውን ክስ ለመካድ አይችሉም ማለት ነው። አ.ት፡ “ልክ በፊት ለፊታችሁ” ወይም “ልትክዷቸው በማትችሉባቸው ሁኔታዎች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እናንተ እግዚአብሔርን የምትረሱ

እግዚአብሔርን የተዉትን ክፉዎች እርሱን እንደረሱት አድርጎ ይናገራል። ስለ ራሱ በሦስተኛ መደብ ይናገራል። አ.ት፡ “እኔን የምትተዉኝ እናንተ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

እሰባብራችኋለሁ

ያደነውን እንደሚበላ አንበሳ እግዚአብሔር ክፉዎችን እንደሚያጠፋቸው ይናገራል። አ.ት፡ “አጠፋችኋለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)