am_tn/psa/050/018.md

1.8 KiB

ከእርሱ ጋር ትስማማለህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) የሌባውን ተግባር ያጸድቃሉ። አ.ት፡ “ታጸድቁታላችሁ” ወይም 2) በተግባራቸው ሌባውን ይተባበሩታል። አ.ት፡ “ትተባበሩታላችሁ” የሚሉት ናቸው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

አፍህን ለክፋት ሰጠህ

ክፉ ነገርን ስለሚናገር ሰው፣ የዚያ ሰው አፍ፣ ክፉ ነገርን እንዲያደርግ ለሚልከው ለእርሱ መልዕክተኛ እንደሚሆን እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “አንተ ሁሌም የምትናገረው ክፉ ነገርን ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Synec- doche የሚለውን ተመልከት)

ምላስህ ማታለልን ይገልጣል

“ምላስ” የሚለው ቃል የሚወክለው ተናጋሪውን ሰው ነው። አ.ት፡ “አንተ ሁልጊዜ ትዋሻለህ” (See: Synecdoche)

ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው፤ የገዛ እናትህን ልጅ ስም አጠፋህ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች የተለያየ ቃል ቢጠቀሙም ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። በቤተሰብ አባሎቻቸው ላይ በሐሰት ስለመናገራቸው እግዚአብሔር ይወቅሳቸዋል። (See: Parallelism)

ተቀምጠህ ተናገርክ

በአንድ ሰው ላይ “ተቀምጠህ ተናገርክ” ማለት ይህ ሰው ስለሌላው ሰው ሆነ ብሎ ክፉ ነገሮችን ያወራል ማለትን ያመለክታል። አ.ት፡ “ሁሌም ስለምትናገርባቸው መንገዶች ታስባለህ” (የአነጋገር ዘይቤ፣ Assumed Knowledge and Implicit Information የሚለውን ተመልከት)